በሰሜን ዕዝ ላይ  የተፈጸመው ጥቃት 2ኛ ዓመት መታሰቢያ መርሐግብር ተካሄደ - National Bank

በሰሜን ዕዝ ላይ  የተፈጸመው ጥቃት 2ኛ ዓመት መታሰቢያ መርሐግብር ተካሄደ

በሰሜን ዕዝ ላይ የተፈጸመው ጥቃት 2ኛ ዓመት መታሰቢያ መርሐግብር ተካሄደ

ጥቅምት 24 ቀን 2015:- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የማኔጅመንት አባላትና ሠራተኞች በሀገር መከላከያ ሠራዊት በሰሜን ዕዝ ላይ የተፈጸመው ጥቃት 2ኛ ዓመት መታሰቢያ መርሐ ግብር አካሄዱ።

“መቼም አንረሳውም!” በሚል መሪ ቃል ጥቅምት 24 ቀን 2015 ዓ.ም በተካሄደው በዚህ መርሐግብር ላይ በግፍ የተሰዉ የአገር መከላከያ ሠራዊት አባላትን ለማሰብ የሕሊና ጸሎት ተደርጓል።

የባንኩ ገዥ ዶክተር ይናገር ደሴ እንደተናገሩት፣ አገርን ሲጠብቅ በነበረ የወገን ጦር ላይ የተፈጸመው ዘግናኝ ጥቃት እስከመቼውም የሚረሳ አይደለም።

የሰሜን ዕዝ የትግራይን ሕዝብ እዚያው አጠገቡ ሆኖ ከጠላት ሲጠብቀው፣ አዝመራውን ሲሰበስብለትና ልዩልዩ ድጋፎች ሲያደርግለት እንደነበር ያስታወሱት ክቡር ገዥ፣ ነገር ግን ሕወሓት በድንገት በፈጸመው ዘግናኝ ግፍ የሕዝቡና የአገሪቱ ጠላት መሆኑን አስመስክሯል ብለዋል።

ክቡር ገዥ አክለውም “ሕወሓት በአፋርና በአማራ ክልሎች በፈጸመው ግፍ በርካታ ሰዎች ገድሏል፤ ለአካል ጉዳት ዳርጓቸዋል፤ ንብረት ዘርፏል፤ መዝረፍ ያልቻለውን ደግሞ አውድሟል፤ እስከመቼውም ሊረሳ የማይችል ሰቆቃ አድርሷል” ሲሉ ገልጸዋል።

በመሆኑም የአገር መከላከያ ሠራዊት ርምጃ ለመውሰድ የተገደደ ሲሆን፣ ጠላትም ከፍተኛ ኪሳራ ደርሶበታል። የኢትዮጵያ መንግሥት ባስቀመጣቸው ነጥቦች መሠረት ስምምነት ፈርሟል። ከእንግዲህ ዜጎችም በእፎይታ የሰላም ኑሯቸውን ይኖራሉ ብለዋል።

“በቀጣይም ሕወሓት የፈለፈላቸውን አማጽያን ከሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች የማጽዳት ትኩረት የሚሠጠው ሲሆን፣ የብልጽግና ጉዟችን በተሳካ ሁኔታ ይቀጥላል፤ የባንኩ ሠራተኞችም የባንኩን ራዕይ ለማሳካት ጥረታቸውን አጠናክረው መቀጠል አለባቸው” ሲሉ ዶክተር ይናገር መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

በሥነሥርዓቱ ላይ ምክትል ገዥዎች፣ ዳይሬክተሮችና ሌሎች የባንኩ ሠራተኞች ተገኝተዋል። የተሰዉትን ጀግኖች ለማስታወስ የአንድ ደቂቃ የሕሊና ጸሎት ተካሂዷል። የኢትዮጵያ ሕዝብ ብሔራዊ መዝሙር ተዘምሯል።

The National Bank of Ethiopia was established in 1963 by proclamation 206 of 1963 and began operation in January 1964.

P.O.Box: 5550
Tel: +251 115 517 430
E-mail: nbeinfo@nbe.gov.et
Fax: +251 115 514 588
Avenue: Sudan Street

Navigation

Follow Us