“የተረጋጋ የውጭ ምንዛሬና ጤናማ የፋይናንስ ሥርዓት እንዲኖር ይሠራል” - National Bank

“የተረጋጋ የውጭ ምንዛሬና ጤናማ የፋይናንስ ሥርዓት እንዲኖር ይሠራል”

የኢትዮጵያ የብሔራዊ ባንክ ገዥ
ኤልያስ ሳላህ

የተረጋጋ ዋጋና የውጭ ምንዛሬ እንዲሁም ጤናማ የፋይናንስ ሥርዓት የማክሮኢኮኖሚ ዕድገት መሠረት በመሆናቸው የኢትዮጵያ የብሔራዊ ባንክ እነርሱ ላይ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሠራ አዲሱ የባንኩ ገዥ አቶ ማሞ እስመለዓለም ምህረቱ ገለጹ፡፡ ከፋይናንስ ዘርፍ የሥራ ኃላፊዎች ጋርም በዘርፍ የ 6 ወር አፈጻጸም ላይ ውይይት አካሂደዋል፡፡ ጥር 24 ቀን 2015 በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲሱ ህንፃ ዋናው አዳራሽ በተካሄደው ውይይት ላይ አቶ ማሞ የፋይናንስ ዘርፉ ብቻውን የቆመ ሳይሆን ከማክሮኢኮኖሚ ጋር ተያይዞ የሚጓዝ መሆን እንዳለበት አመልክተዋል፡፡ በዚህ ዓመት በ 7 ነጥብ 5 በመቶ ያድጋል ተብሎ ለሚጠበቀው የአገሪቱ ኢኮኖሚ የፋይናንስ ሴክተሩ የራሱ አስተዋጽኦ እንደሚኖረውም ጠቁመዋል፡፡ የባንኩ ዋነኛ ተልዕኮዎች የሆኑትን ዋጋ የማረጋጋትና የውጭ ምንዛሬ ተመን የማስፈን እንዲሁም ጤናማ የፋይናንስ ሥርዓት የመፍጠር ጥረት በቀጣይ የባንኩ ዋነኛ ትኩረቶች እንደሚሆኑ የጠቆሙት አቶ ማሞ፣ በቀጣይም የዋጋ ንረትን እንዳያባብስ በገንዘብ ፖሊሲው አማካኝነት የተጠና ሥራ እንደሚሠራም አስታውቀዋል፡፡ የፋይናንስ ዘርፉ በአጠቃላይ፣ በተለይም የባንክ ዘርፉ በአገር ዕድገት ላይ እያደረገ ያለውን አስተዋጽኦ ያነሱት ዋና ገዥው፣ ለአብነትም ባለፉት ስድስት ወራት ከ157 ቢሊዮን ብር በላይ የግምጃ ቤት ሰነድ መግዛቱን አመልክተዋል። ይህም የበጀት ጉድለትን በመሙላት ረገድ የፋይናንስ ዘርፍ ከጊዜ ወደ ጊዜ ያለው አስተዋጽኦ እየጨመረ መሆኑን እንደሚያሳይ የጠቆሙት አቶ ማሞ፤ ባንኮች የሚሰበስቡት የተቀማጭ ገንዘብ፣ ሃብትና የሚሰጡት ብድር በየዓመቱ በአማካይ በ30 በመቶ እያደገ ስለመሆኑም ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅት ከባንክ ውጭ ያለው ገንዘብ ከ189 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱን ጠቁመው ይህም ለባንኮች ተጨማሪ ሃብት ለማሰባሰብ እድል የሚፈጥር እንደሆነ አመልክተዋል፡፡

The National Bank of Ethiopia was established in 1963 by proclamation 206 of 1963 and began operation in January 1964.

P.O.Box: 5550
Tel: +251 115 517 430
E-mail: nbeinfo@nbe.gov.et
Fax: +251 115 514 588
Avenue: Sudan Street

Navigation

Follow Us