አዲስአበባ፣ ነሐሴ 11 ቀን 2013 ዓ.ም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሠራተኞች ለአገር መከላከያ ሠራዊት የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታወቁ።
የባንኩ ማኔጅመንት አባላትና መላ ሠራተኞች ዛሬ ባካሄዱት ስብሰባ ለጀግናው መከላከያ ሠራዊታችን የሚሆን ከደጀንነት እስከ ግንባር መሰለፍ የሚደርስ አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል።
ሠራተኞቹ የአንድ ወር ደመወዛቸውን ከ15 ሚሊዮን ብር በላይ ሠጥተዋል።
ከዚህ በተጨማሪ ቀደም ሲል ሲያደርጉት እንደቆዩት ሁሉ ደም መለገሳቸውን እንደሚቀጥሉበት አረጋግጠዋል።
ሠራተኞቹ ከደጀንነት በተጨማሪ ግንባር ድረስ በመሄድ ከሠራዊቱ ጎን በመሰለፍ የሕይወት መስዋዕትነት ለመክፈል መዘጋጀታቸውንም አስታውቀዋል። ወደ ግንባር ለመዝመት ተመዝግበው ለመሄድ የተዘጋጁ የባንኩ ባልደረቦች መኖራቸውም ታውቋል።
ሠራተኞቹ ለሠራዊቱ በቀጥታ ከሚያደርጉት ድጋፍ ጎን ለጎን በተሠማሩበት የሙያ መስካቸው የበለጠ በመትጋት ኃላፊነታቸውን እንደሚወጡም አረጋግጠዋል።