የኤግዝኪዩቲቭ ማኔጅመንት አባላት የችግኝ ተከላ አካሄዱ

የኤግዝኪዩቲቭ ማኔጅመንት አባላት የችግኝ ተከላ አካሄዱ

ሐምሌ 5 ቀን 2014 ዓ.ም:- በባንኩ ገዥ ዶክተር ይናገር ደሴ የሚመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የኤግዝኪዩቲቭ ማኔጅመንት አባላት የአራተኛውን የአረንጓዴ አሻራ መርሐግብር መሠረት በማድረግ የችግኝ ተከላ አካሄዱ።

ትናንት ሐምሌ 5 ቀን 2014 ዓ.ም አቃቂ/ቃሊቲ በሚገኘው የኢትዮጵያ የፋይናንስ ጥናት ተቋም በተካሄደው በዚህ መርሐግብር የኤግዝኪዩቲቭ ማኔጅመንት  አባላት ክቡር ገዥ ዶክተር ይናገር ደሴ፣ አቶ ፈቃዱ ድጋፌ፣ የባንኩ ምክትል ገዥና ዋና ኢኮኖሚስት፣ አቶ ሰሎሞን ደስታ፣ የፋይናንስ ተቋማት ሱፐርቪዥን ምክትል ገዥ፣ አቶ እዮብ ገብረየሱስ የኮርፖሬት ሰርቪስ ምክትል ገዥ እንዲሁም አቶ አባተ ምትኩ የለውጥ ማኔጅመንት፣ ዕቅድና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር ተሳትፈዋል።

በተጨማሪም አዲስ ተቀጣሪ ጁኒየር ኦፊሰሮችና የትውውቅ ሥልጠና ተሳታፊዎች፣ እነርሱን የሚያሰለጥኑ ኃላፊዎች፣ የተቋሙ ኃላፊዎችና ሠራተኞች የችግኝ ተከላ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት፣ ሌሎችም በተለያዩ አጋጣሚዎች በማሠልጠኛ ተቋሙ ውስጥ የተገኙ ሰዎች የተዘጋጁትን ችግኞች ተክለዋል።

በዘንድሮውና ቀደም ባሉት ዓመታት በተካሄዱት የአረንጓዴ አሻራ መርሐግብሮች ከ10ሺ በላይ የተለያዩ አገር በቀልና የውጭ ዝርያ ያላቸው ዛፎች፣ ለምግብነት የሚውሉ ፍራፍሬና ለውበት የሚሆኑ የአበባ ችግኞች በተቋሙ ውስጥ ተተክለዋል።

በቅርቡም ለምግብ የሚሆኑ እንደቆስጣ፣ ሰላጣ፣ ጥቅል ጎመን፣ ቲማቲም፣ ድንች፣ ካሮትናሌሎችንም አትክልቶች በማልማት ለተቋሙና ለዋናው የባንኮች ክበብ ማቅረብ ተችሏል።

ለተተከሉት ችግኞች ዘወትር እንክብካቤ የሚያደርጉ ባለሙያዎች በመመደባቸው ችግኞቹ ጸድቀው በፍጥነት ያደጉ ሲሆን፣ አበቦቹ ደግሞ ለተቋሙ ምድረግቢ ልዩ ውበት ሰጥተውታል።

ችግኞቹ ከሰውና ከእንስሳት ንኪኪ ነጻ በመሆናቸው ዕድገታቸው ፈጣን ከመሆኑም በላይ ለችግኞቹ በሚደረገው እንክብካቤ ሳቢያ ጠፍተው የነበሩና ልዩ ዝርያ ያላቸው ሌሎች የተክል ዓይነቶች መብቀል ችለዋል።  

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሠራተኞች በአረንጓዴ አሻራ መርሐግብር መሠረት ከተከሏቸው ችግኞች በተጨማሪ ባለፈው ዓመት ለልደታ ክፍለከተማ የ200ሺህ ብር እንዲሁም ዘንድሮ ደግሞ ለአቃቂ/ቃሊቲ ክፍለከተማ የ100ሺህ ብር ችግኞችን ገዝቶ በማስረከብ ለመርሐግብሩ ስኬት ባንኩ የድርሻውን በመወጣት ላይ ይገኛል።

The National Bank of Ethiopia was established in 1963 by proclamation 206 of 1963 and began operation in January 1964.

P.O.Box: 5550
Tel: +251 115 517 430
E-mail: nbeinfo@nbe.gov.et
Fax: +251 115 514 588
Avenue: Sudan Street

Navigation

Follow Us