የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከተጣለበት ትልቅ ሀገራዊ ሀላፊነት አኳያ አቅሙን አጎልብቶ በርካታ ትላልቅ ተግባራት ማከናወን እንዳለበት የባንኩ ገዥ ዶ/ር ይናገር ደሴ ገለፁ፡፡ አዲስ ከተሾሙት ም/ ገዥዎችና ዳይሬክተሮች ጋርም የትውውቅ መድረክ ተካሂዷል፡፡ መስከረም 29 ቀን 2012 ዓ.ም በባንኩ የቦርድ አዳራሽ በተካሂደው የሲኒየር ማኔጅመንት ስብሰባና የትውውቅ መድረክ ላይ ክቡር ገዥው እንዳሉት ባንኩ ጠንካራ ሥራ ማከናወን የለውጥ ሂደቱን ማሳካት ያስችለው ዘንድ ነባር አመራር አባላትን በአዲስ በመተካት በአዲስ ሀይል አቅሙን ማሳደግ ይጠበቅበታል፡፡