የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የ2018 ዓ.ም የመጀመሪያው ግማሽዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፕላን፣ የበጀት አና የፋይናንስ ቋሚ ኮሚቴ አቀረበ።

ጥር 25 ቀን 2018 ዓ.ም፤ አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የ2018 ዓ.ም የመጀመሪያው ግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፕላን፣ የበጀትና የፋይናንስ ቋሚ ኮሚቴ አቅርቧል። በበጀት ዓመቱ በስድስት ወራት ውስጥ የዋጋንና የውጭ ዘርፍን በማረጋጋት፣ የተረጋጋ ፋይናንስ ስርዓት በማስፈን እና ዲጂታል ክፍያ እድገትን በማምጣት ረገድ ከፍተኛ ስራዎች ተሰርተዋል።

ከዚህ ውስጥም ዋና ዋና ስኬቶችን ስንመለከት:-

  • ጠቅላላ የዋጋ ግሽበት በከፍተኛ መልኩ ቀንሶ 9.7 ደርሷል። በዚህም ረገድ ብሔራዊ ባንክ በበጀት ዓመቱ የዋጋ ግሽበትን ወደ ነጠላ አሀዝ የማውረድ ዕቅድን ማሳካት ቸሏል፡፡
  • የውጭ ምንዛሪ ክምችት በከፍተኛ ሁኔታ ማሳደግ ተችሏል፣ በተጨማሪም የተጣራ የግል ሐዋላ አምና በተመሳሳይ ወቅት ከነበረበት በ36.5 በመቶ እድገት እሳይቶ 4.6 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል፡፡
  • የፋይናንስ ተቋማት ጤናማነት በበርካታ መለኪያዎች በእጅጉ ተሻሽሏል፡፡ የባንኮች የውጭ ምንዛሪ ክምችትና ጠቅላላ ተቀማጭ ገንዘብም በከፍተኛ መልኩ ጨምሯል።
  • በባንክ ዘርፍ የተቀማጭ ገንዘብ ክምችት 4.2 ትሪሊዮን ብር የደረሰ ሲሆን ይህም ከአምና በተመሳሳይ ወቅት የ44.6 በመቶ እድገት አሳይቷል።
  • በባንኮች የተሰጠ ጠቅላላ ብድርም 2.42 ትሪሊዮን ብር ሆኖ ከ45 በመቶ በላይ እድገት አሳይቷል። የብድር ክምችትን ስናይ 94.5 በመቶው በግል ድርጅቶች የተያዘ ሲሆን ይህም ለዘርፉ እየተሰጠ ያለውን ድጋፍ ማሳያ ነው።
  • የዲጂታል ክፍያዎች በዋጋ ወደ 14.56 ትሪሊዮን ብር የደረሱ ሲሆን ይህም የ94 በመቶ በላይ እድገት አሳይቷል። የዲጂታል አካውንት ብዛትም ከ20 በመቶ በላይ እድገት አሳይቷል።

በቀጣይም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የትኩረት አቅጣጫዎች የሚሆኑት የዋጋ ንረትን ነጠላ አሀዝ ሆኖ ማቆየት፤ የውጭ ምንዛሪ አስተዳደር ስርዓትን ማስፈን እና ማስረጽ፤ ዲጂታል ፋይናንስ ስርዓት ማሻሻል፤ የባንክ ዘርፍ ተወዳዳሪነትን መጨመር፤ እናም ከተቋማት ጋር የፖሊሲ ቅንጅትና ትብብርን ማጠናከር ይሆናሉ።

More News