የ2018 አመታዊ የፋይናንስ ዕውቀት ሳምንት ማስጀመሪያ ስነስርዓት

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከጋምቤላ ክልላዊ መንግሥት፣ከኒውፊን ኢትዮጵያ (NewFin) እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ካፒታል ልማት ፈንድ (UNCDF Ethiopia) ጋር በመተባበር ከጥቅምት 17 እስከ 21 ቀን 2018 ዓ.ም የሚቆየውን የመጀመሪያ የሆነውን “ዓመታዊ የፋይናንስ ትምህርት ሳምንት 2018” በዛሬው ዕለት ጥቅምት 17 ቀን 2018 ዓ.ም መጀመሩን ይፋ አደረገ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ አግልግሎት ዕውቀትን ለማሻሻል፣የፋይናንስ አካታችነትን ለማሳደገ እና  የዜጎችን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል እ.አ.አ ከ 2021 ጀምሮ በብሔራዊ የፋይናንስ ትምህርት ስትራቴጂ ትግበራን የማበረታታት፣ የመምራት እና የማስተባበረና  እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል።በዚህ ስትራቴጂ ከሚተገበሩ የፋይናንስ ትምህርት እንቅስቃሴዎች መካከል ዋነኛው በብሔራዊ ባንክ አስተባባሪነት  በፋይናንስ ተቋማት፣ በፌዴራል እና በክልል የመንግስት አካላት እና በልማት አጋር ድርጅቶች ጥምረት የገጠር ሴቶችንና ወጣቶችን ትክረት ያድረገ የፋይናንስ ትምህርት የቅስቀሳ ሳምንት ዘመቻ አንዱ ነው።

በዚህም መሠረት የ2018 ዓ.ም አመታዊ የፋይናንስ ዕውቀት ሳምንት “የፋይናንስ እውቀትን ማጎልበት እና የፋይናንስ ደንበኞች ጥበቃን ማጠናከር” በሚል መሪ ቃል የሚከናወነውን በዋነኝነት የገጠር ሴቶችንና የወጣቶችን በመረጃ ላይ የተመሰረተ የፋይናንስ ውሳኔን እና የፋይናንስ ደህንነትታቸውን ለማጠናከር ያለመ ነው። በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስተባባሪነት የሚከናወነው ይህ የፋይናንስ ዕውቀት ሳምንት የፋይናንስ ተቋማት እና የክልል የፋይናንስ አካታችነት ምክር ቤቶች አባል ቢሮዎች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የፋይናንስ ትምህርት ተግባራት በማከናወን ኋላፊነታችወን ይወጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

  • የፋይናንስ ዕወቀት ሳምንት በጋምቤላ ከተማ የመክፈቻ ስነስርዓት ማከናውን
  • በሁሉም ክልሎች የሚገኙ የፋይናንስ ተቋማት ቅርንጫፎች እና የመንግስት ቢሮዎች ብሔራዊ ባንክ ባስቀመጠው ዲዛይንና ይዘት መሰረት ባነሮችን ማሳየት።
  • ዝቅተኛ የፋይናንስ እውቀት ያላቸውን ማህበረሰቦችን በየቅርጫፎቻቸው ቅስቀሳ በማድረግ የሞባልይ አካውንት እንዲከፍቱ ማበረታታት
  • የፋይናንስ አገልግሎት የግንዛቤ መልእክቶችን በመንገድ ትዕይንት፣ በአጭር የጹሁፍ መልእክት፣ በበራሪ ወረቀቶች ፣በመገናኛ ብዙኃን እና በማህበራዊ ሚዲያ  ማሰራጨት።
  • በጋምቤላ ከተማ ለሚገኙ ዝቅተኛ የፋይናንስ ዕውቀት ላላቸው ሲቶች ዜጎች በጋምቤላ ከተማ የፋይናንስ ትምህርት ስልጠና መስጠት
  • በጋምቤላ ከተማ ለሚገኙ የፋይናንስ ተቋማት ሰራተኞች በደንበኞች አያያዝ እና ጥበቃ ላይ ስለጠና መስጠት፣ እና
  • ለባንክ ባላሙያዎች እና ወጣቶች የኬሪየር ደቨሎፕመንት ስልጠና መስጠት ይገኙበታል።

በእነዚህ የተቀናጁ ጥረቶች በአገር አቀፍ ደረጃ ወደ ሦስት ሚሊዮን የሚጠጉ ጎልማሶች (50% የሚሆኑት ሴቶች) የሞባይል ገንዘብ ሂሳቦችን መክፈት ስለመቻልና እና መጠቀም ስለሚያስገኛቸው ጥቅሞች ይማራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

More News