ጋዜጣዊ መግለጫ | ፍቃድ ያላቸው የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶችንበመጠቀም ዙሪያ የተሰጠ ማሳሰቢያ

ታኅሣሥ 20 ቀን 2018 ዓ.ም አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ
በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ፍቃድ የሌላቸው የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶችን እና ሌሎች ህገ-ወጥ የሐዋላ አስተላላፊዎችን መጠቀም በሀገሪቷ ህግ የተከለከለ ሲሆን፣ በሀገር ውስጥ ያሉ የህገ-ወጥ ሐዋላ ተቀባዮችም ላይ ችግር ያስከትላል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በህግ በተሰጠው ስልጣን መሰረት ፍቃድ በሌላቸው የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶች ላይ ብቻ ሳይሆን በሀገር ውስጥ ህገ-ወጥ የውጭ ምንዛሪ ተቀባዮች ላይም እርምጃ እየወሰደ ነው።

በዚህ ሂደት ከውጭ የሐዋላ ገንዘብ የሚልኩላቸውን የቤተሰብ አባላትና ወዳጆችን ከአላስፈላጊ እንግልት እና የአገልግሎት መስተጓጎል ለመጠበቅ ውጭ የምትኖሩ ዜጎች እና የኢትዮጵያ ዲያስፖራ አባላት ፍቃድ ያላቸውን ተቋማትን ብቻ እንድትጠቀሙ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አጥብቆ ያሳስባል።

ለምሳሌ እንደ ሸጌ፣ አዱሊስ(ADZ)፣ ሬድ ሲ፣ አቫንቲ፣ ወርልድ ዳይሬክት ሊንክ፣ ራስማይ ፔይ፣ ዩኤስ ዋየር፣ ዞላ፣ እና ታጅ የመሳሰሉ የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶች በኢትዮጵያ ሕጋዊ ፍቃድ የሌላቸው ድርጅቶች መሆናቸው ሊታወቅ ይገባል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ፈቃድ የተሰጣቸው የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶች ስም ዝርዝር በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ድረ-ገጽ nbe.gov.et/mta ላይ ይገኛል።

More News