ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የተሰጠ መልዕክት

ነሐሴ 28 ቀን 2017 ዓ.ም አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ክቡር ገዢ አቶ ማሞ ምህረቱ በስራ ዘመናቸው ላበረከቱት ልዩ አመራርና ላሳዩት የአገልግሎት ቁርጠኝነት ልባዊ ምስጋናውን ይገልፃል። ክቡር ገዢው በኃላፊነት በነበሩበት ወቅት ለበርካታ ዓመታት ሲጠበቁ የነበሩ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሞችን ተግባራዊ አድርገዋል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ክቡር ገዢ አቶ ማሞ ምህረቱ ላሳዩት ከፍተኛ የሆነ የአመራር ጥበብ እና ቁርጠኝነት የተሰማውን ጥልቅ ምስጋና እየገለጸ የወደፊት የሥራ ዘመናቸው ስኬታማ እንዲሆን ልባዊ ምኞቱን ይገልጻል።

More Archive