ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የተሠጠ መግለጫ

እንደሚታወቀው በቀጣዮቹ ቀናት በአገራችን የመውሊድ፣ የመስቀል፣ የኢሬቻና ሌሎች በዓላት በተከታታይ ይከበራሉ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ሁሉም እንደየእምነቱ በዓሉን በደስታ ለማሳለፍ በስፋት በግብይት ላይ እንደሚሳተፍ ይታወቃል፡፡ ይህንኑ አጋጣሚ በመጠቀም ወንጀለኞች በቻሉት መንገድ ሁሉ ሀሰተኛ ገንዘቦችን በማሳተምና በማሰራጨት በበዓላት ወቅት ግብይት ላይ ለማዋል ጥረት በማድረግ ላይ መሆናቸውን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በመሆኑም፣ ሕብረተሰቡ በግብይት ወቅት በሀሰተኛ ገንዘቦች ክፍያ ምክንያት ሊያጋጥም ከሚችል ያልታሰበ ጉዳት ራሱን መጠበቅ ይኖርበታል፡፡


ስለሆነም፣ በሁሉም ገንዘቦች ላይ የሚገኙ የደህንነት መጠበቂያ ምልክቶችን በትኩረት በመመልከት፣ ለግብይት በሚቀርቡላችሁ ገንዘቦች ላይ ከሚታዩ ምልክቶች ጋር በማነፃፀር ሕገ-ወጦች ከሚያዘዋውሩት ሐሰተኛ ገንዘቦች ራሳችሁን እንድትጠብቁ በአጽንኦት እናሳስባለን፡፡ ከዚሁ ጋር ሐሰተኛ ገንዘቦችን የሚያትሙ፣ የሚያዘዋውሩና ለመገበያየት የሚያቀርቡ ወንጀለኞችን በአካባቢው ለሚገኙ የፀጥታ አካላት ወዲያውኑ በመጠቆም ወንጀሉን ለመከላከል የበኩላችሁን አስተዋፅኦ እንድታደርጉ ባንኩ ጥሪ ያቀርባል፡፡

More News