ወደ ቻይና ሕዝባዊ ሪፐብሊክ የሚላኩ ምርቶች የወጪ ንግድ (EXPORT)ፈቃድ በሁሉም ባንኮች እንዲሰጥ በተመለከተ የወጣ መግለጫ

ግንቦት 18 ቀን 2018 ዓ.ም፤ አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት ከቻይና ሕዝባዊ ሪፐብሊክ መንግሥት ጋር በነበረው አጠቃላይ የኢኮኖሚና የፋይናንስ ትብብር ስምምነት መሠረት ወደ ቻይና የሚላኩ ምርቶች የወጪ ንግድ ፈቃድ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE) ብቻ እንዲሰጥ ቀደም ሲል በቁጥር ባውምዳ/097/99 በጻፈው ደብዳቤ መወሰኑ ይታወሳል።

ነገር ግን የሀገሪቱን የወጪ ንግድ ዘርፍ ይበልጥ ለማቀላጠፍ ተወዳዳሪነትን ለማሳደግ እና ለላኪዎች ምቹና ተደራሽ የባንክ አገልግሎት ለመፍጠር ሲባል ይህ ቀደም ሲል ተጥሎ የነበረው ገደብ ሙሉ በሙሉ የተነሳ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

በመሆኑም ከዛሬ ግንቦት 18 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ ወደ ቻይና ሕዝባዊ ሪፐብሊክ የሚላኩ ማናቸውም የኤክስፖርት ምርቶች የፈቃድ አሰጣጥ ሰነድ ማደራጀትና ተያያዥ የባንክ አገልግሎቶች በሀገሪቱ ውስጥ ፈቃድ ባላቸው በሁሉም ባንኮች በኩል መስተናገድ የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን ሁሉም የንግድ ባንኮች ከተለመዱት የወጪ ንግድ እና የውጭ ምንዛሪ መመሪያዎች ጋር በተጣጣመ መልኩ ለደንበኞቻቸው አገልግሎቱን እንዲሰጡ እናሳስባለን።

More News