የኃላፊነት ማስተባበያ (DISCLAIMER)

እባክዎ ይህ የቃለ-ጉባዔ ናሙና ከመጠቀምዎ በፊት ይህንን የኃላፊነት ማስተባበያ (DECLAIMER) በጥንቃቄ ያንብቡ!

ይህ የቃለጉባዔ ናሙና፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አግባብነት ባላቸው ሕጎች በተሰጠው ሥልጣንና ተግባራት መሰረት የፋይናንስ ተቋማት በመቆጣጠር እና በመከታተል ሂደት የሥራ ቅልጥፍና ጥራት ለማምጣት በማሰብ የተዘጋጀ ሆኖ የዚህ የቃለጉባዔ ናሙና ተጠቃሚው በሌላ ተቆጣጣሪ ወይም አገልግሎት ሰጪ ወይም ሌላ መንግስታዊ የአስተዳደር ተቋም በሚጠይቀው አግባብ ለመጠቀም ሲፈልግ ለዚሁ ተግባር በትክክል ናሙናውን ተስማሚ፣ ሙሉነት ያለው እና ወቅታዊነቱን የጠበቀ ስለመሆኑን የማረጋገጥ እና አስፈላጊ ማሻሻያዎችን የማድረግ ሙሉ ኃላፊነት አለበት፡፡

ይህ የቃለጉባዔ ናሙና ወይም በውስጡ የተገለጸውን መረጃ በማናቸውም አግባብ በመጠቀም ምክንያት ስለሚከተለውን ማንኛውም ቀጥተኛም ሆነ ቀጥተኛ ያልሆነ ኪሳራ፣ ጉዳት ወይም ተጠያቂነት የሚያስከትል ከሆነ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ምንም ዓይነት ኃላፊነት አይወስድም፡፡ በተጨማሪ የቃለጉባዔ ናሙናው ያለቅድመ ማስጠንቀቂያ በማንኛውም ጊዜ ሊሻሻል፣ ሊቀየር ወይም ሊወገድ ይችላል፡፡